መማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ
መማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት እና የተቋማት ብቃት በማስጠበቅና የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ተግባራዊ በማድረግ የመማር ውጤታማነትና የተማሪዎች ባህርይ ማሻሻል ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡ እንዲሁም የተማሪዎች የመማር ብቃትና በትግበራ ላይ ያለውን ሥርዓተ ትምህርቱን ውጤታማነት የመመዘን እና የትምህርት ጥናት የማድረግ ሥራን ይመራል፡፡ ደግሞም በጎልማሶችና መደበኛ ባልሆነ የትምህርት ፕሮግራም፣ የትምህርት ዕድል ያመለጣቸውና በመደበኛው መርሃ ግብር መማር የማይችሉ ዜጎች መደበኛ ባልሆኑ አማራጮች መማር እንዲችሉ በማድረግ ላይም ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡
1 የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይረክቶሬት
- የሥራ ክፍሉ ዋና ዓላማ
- ግልፅና ወጥ በሆነ መለኪያ ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ሁኔታ በመገምገም መረጃን መሠረት ያደረገና ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ የትምህርት ፍትሀዊነትን ያረጋገጠ የትምህርት ቤት መሻሻል ዕቅድ በማዘጋጀት፤ በመተግበርና በመገምገም የተማሪዎችን የመማር ዉጤትና ስነ-ምግባር ማሻሻል ነዉ፡፡
2 የጎልማሳና መደበኛ ያልሆነ ትም/ት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት
.የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትም/ት ግብ ዕድሜያቸው 15 ዓመትና ከዛ በላይ የሆናቸው ወጣቶችና ጎልማሶች መሠረታዊ የጎልማሶች ትም/ት በማግኘት ጎልማሶው ማንበብ፣ መፃፍ ማሰላት እንድችሉ ማድረግና ዜጎች በመደበኛው ትም/ት ፕሮግራም የመማር እድል ላላገኙ ህፃናትና ወጣቶች መደበኛ ያልሆነ የትም/ት መርሃ-ግብርን እንደ አንድ አማራጭ የትምህርት አቅርቦት በመጠቀም ዜጎች በዕውቀት፣በክህሎትና በአስተሳሰብ የደበሩና አዳዲስ ተክኖሎጂዎችን በመጠቀም የኑሮ ደረጃቸውን እንድያሻሽሉ በማስቻል የሀገራችን መሠረታዊ ትምህርት ምጣኔ ማሳደግ ነው፡
3 የአጠቃላይ የትምህርት ሱፔርቪዥንና የተቋማት ብቃት ማረጋገጥ አላማ ተኮር ዳሬክቶሬት
ዓላማ
የዳይሬክቶሬቱ ዓላማ ዜጎች ለደረጃዉ ብቁ በሆኑ ትም/ቤቶች ቤቶች ተምረዉ ብቁ ዜጋ መሆን ይችሉ ዘንድ ከትምህርት ስታንዳርድ አንፃር የትምህርት ተቋማት ብቃት ደረጃ ማረጋገጥና የትም/ቤቶችን ዕቅድ አፈጻጸም መከታልና መደገፍ ነዉ
4 የፈተና ዝግጅት ፤አስተዳደር ፤ የትምህርት ምዘናና ጥናት ተግባር ተኮር ዳይሬክቶሬት
የፈተና ዝግጅት አስተዳደርና የትምህርት ምዘናና ጥናት ዳይሬክቶሬት ዋና ዋና ተግባራት
- ያለፈውን ዓመት ዕቅድ አፈጻጻም በመገምገም የቀጣዩን ዓመት እቅድ በማዘጋጀት ለሚመለከታቸዉ አካል ማቅረብ፤
- የ2015 ዓ.ም የበጀት ዘመን ዉጤት ተኮር እቅድ አዘጋጅቶ ማቅረብ፤
- የበጀትና የእቅድ አፈፃፀም፤አጠቃቀምና ዉጤታማነትን ማሳደግ፤
- የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ማሽቆልቆል ጋር ተያይዞ ዝግጅትና አስተዳደር ይኖራሉ ተብሎ በሚታሰቡ ችግሮች ላይ ጥናትና ምርምር ማድረግ፤
- በፈተና ዝግጅትና አስተዳደር፣ በትም/ምዘና ጥናት ላይ በክልሉ ዉስጥ ካሉት አካባቢዎችና ከክልሉ ውጭ ጉብኝት በማድረግ በልምድ ልዉዉጥ ምርጥ ተሞክሮችን ለይቶና ቀምሮ ማሰራጨት፤
- የተፈታኞች መመዝገቢያና ተያያዥ ቅጻቅጾች አጠቃቀምና አመዘጋገብ ላይ ለዞንና ለወረዳ ባለሙያዎች ስልጠና የሚሰጥበት የአፈጸጸም ማኑዋል እንዲዘጋጅ በማድረግ ስልጠና መስጠት፤
- በወጥ ፈተና አዘገጃጀት ላይ በስፔሲፊኬሽን እና ጥያቄ አዘገጃጀት የፈተና ዝግጅት አስተዳደርና የትምህር ትምዘና ለርዕሰ መምህራንና ለሱፐርቫይዘሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት፤
- የሀገር አቀፍ ፈተናዎችን ለሚያስፈጽሙ ጣቢያ ሀላፊዎች፤ ሱፐቫይዘሮችና ፈታኞች ድልድል በማዘጋጀት ምደባ እንደአግባቡ መስጠት፤
- አዲስ ዕውቅና የተሰጣቸው የ12ኛ ክፍል አስፈታኝ ትምህርት ቤቶችን መረጃ በማደራጀት ለሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንስ ማስተላለፍ፤
- ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳድር ትምህርት ጽ/ቤት የተመዝጋቢዎች መረጃ በማሰባሰብ በየትምህርት ቤቱ የመጀመሪያ ደረጃ ማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ማጠቃለያ መስራት፤
- ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ሀገር አቀፍ ፈተና በሚመለከት የማስፈፀሚያ ሰነድ በማዘጋጀት የንቅናቄ ምክክር ስብሰባ ማካሄድ፤
- ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ሀገር አቀፍ ፈተና አስተዳደራዊ ድጋፍ ለሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳድር መስጠት፤
- የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚያስፈትኑ አዲስና ነባር ትም/ ቤቶችንና የተፈታኝ ተማሪዎችን ግምታዊ መረጃ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳድር በማሰባሰብና በማጠናቀር ለሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ መግለጽ፤
- የየሩብ አመቱ እቅድ ክንዉን ሪፖርት በጥራት አዘጋጅቶ ማቅረብ፤
- የ8ኛ ክፍል ድጋሚ የትምህርት ማስረጃ ማውጣት ለተገልጋዩ መስጠት፤
- የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ (Authenticate)
- በሀገር አቀፍና የስምንተኛ ክፍል ከልላዊ ፈተና እርማት ውጤትና ተግባራት ዙሪያ የተከናወኑ ስራዎችና የተገኙ፤ ውጤቶችን መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ መተንተንና በማደራጀት በጥንቃቄ ይዞ ጥቅም ላይ ማዋል፡፡
- በሥራ ሂደቱ በታቀዱና በተጠኑ ስራዎች ላይ በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ የድጋፍ፤ የክትትልና የአፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ፤
- በሥራ ሂደቱ በተከናወኑ የድጋፍ፤ የክትትልና የአፈፃፀም ግምገማ ዉጤቶ ላይ ለዞኖችና ወረዳዎች የምክክር መድረክ በማዘጋጀትና በጽሁፍ ግብረ መልስ መስጠት፤
- ሳምንታዊ እቅድ እና ሪፖርት አቀራረብ ሳይቆራረጥ ማካሄድ፤
- የስራ ሂደቱን ተግባራትን አፈፃፀም ለማሻሻል ታቅዶ የተከናወነ የመልካም አስተዳደር ተግባራት ዕቅድ፣ ውይይትና ሪፖርት፤