1 የስርዓተ ትምህርትና ዝግጅት ዘርፍ ኃላፍ
የስርዓተ ትምህርትና መከታተያ ማስፋፋት ዘርፉ የመማር ማስተማሩ ሂደቱ በስርዓተ ትምህርት ታግዞ ወቅታዊና ድጅታል ቴክኖሎጅን ባቀፈ መልኩ በአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ የምኖረዉ ሚና እጅግ በጣም የላቀ እንደሆነ ይታመናል፡፡
ስለሆነም በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ደረጃ ከባለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መነሻ በማድረግ ከቅድመ አንደኛ እስከ 8ተኛ ክፍል ድረስ እና ከ9ኛ-10ኛ ክፍል በሲዳሙ አፎ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ስራዉ ተጠናቆ በ2015 ዓ.ም ሙሉ ትግበራ ዉስጥ የተገባ ሲሆን ይህም በቀጣይ የትምህርት ስርዓቱን ሂደት ዉጤታማ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳሌ እንደ ቢሮ ከተያዘዉ እቅድ አንዱና ዋነኛዉ በሴክቴር ደረጃ የሚከወኑ ተግባራትን ለማህበረሰቡ
በቀላል መንገድ ተደራሽ ለማድረግ የቢሮዉን ዌቢ ሳይት ማደራጄትና ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ሲሰራ የነበረዉ ሂደት ዉጤታማ ሆኖ በማዬቴ ታላቅ ደስታ የተሰማኝ መሆኑን እየገለጽኩ እንደ ዘርፍ ለማህበረሰቡ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ባለዉ ሁኔታ በዝርዝር ቀርበዋል፡፡
ሀ.የዳይረክቶሬቱ ስያሜ፡- የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት፣ ትግበራና የትምህርት መሣሪያዎች አቅርቦት ዓላማ ተኮር ዳይረክቶሬት
በዳይረክቶሬቱ የሚተገበሩ ተግባራት፡-
- ከቅድመ አንደኛ እስከ 8ኛ ክፍሎች የመደበኛ ስርዓተ ትምህርት የይዘት ፍሰት (የፍሎው ቻርት) እና መርሃ ትምህርት ማስማማት
- በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጀውን መርሀ-ትምህርት መሠረት ያደረገ መደበኛ ላልሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች መማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍት እንዲሁም ሞጁሎችን ማዘጋጀት
- ለሁለተኛ ደረጃ ትም/ቤቶች (9-10) የሲዳሙ አፎ መማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍትን ማዘጋጀት
- የመማሪያና ማስተማሪያ እንድሁም አጋዥ መጽሐፍት ማዘጋጀት ፣ማስማማት፣ መተርጎም፣ መከለስና ማስተዋወቅ፣ ማሳተምና ማሰራጨት
- የስርዓተ ትምህርት ትግበራ ክትትልና ግምገማ መድረግ
- በተለያዩ ጉድለቶች የዝግጅትና ትግበራ ላይ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ማከናወን
- የቤተ-ሙከራ፣ የቤተ-መጽሐፍትና የቅርንጫፍ ማዕከላት አገልግሎት ተግባራትን ማከናወን
- ለሬድዮ ትምህርት ፕሮግራም መርሃ ትምህርት፣ ስክሪፕትና የመምህሩ መምሪያ ማዘጋጀት
- የትምህርት በሬድዮ ፕሮግራም አጠቃቀምና አተገባበር ክትትልና ግምገማ ማድረግ
- የስርዓተ ትምህርት ግምገማና የማሻሻል ተግባራትን ማከናወን
- ሥርዓተ ትምህርትን የተመለከቱ የጥናትና ምርምር ተግባራትን መፈጸም
- የተበላሹና ከሥርዓተ ትምህርት ውጪ የሆኑ የትምህርት መጽሐፍትና መሣሪያዎች እንዲሁም ኬሚካሎች የሚወገዱበትን ሁኔታ ማመቻቸት
- በሥርዓተ ትምህርት ዙሪያ ምርጥ ተሞክሮዎችን መለየት፣ መቀመርና ማስፋት
- ከባለድርሻ አካላት ጋር በስርዓተ ትምህርት ዙሪያ የምክክርና የግምገማ መድረኮችን ማካሄድ
- የትምህርት መጽሐፍትና መሣሪያዎች ፍላጎት መለየትና ማደራጀት፤የፍላጎት ጥያቄውንም አደራጅቶ ማቅረብ
- የትምህርት መሣሪያዎችና መጽሐፍት የጨረታ ሰነድ፣ ስፔሲፊኬሺን ማዘጋጀትና ማረጋገጥ፤ማሳተምና ማሠራጨት
- የትምህርት መሣሪያዎች / ኬሚካሎች፣ አፓራተሶችና የሳይንስ ኪቶች ማቅረብ መደልደልና ማሰራጨት/
- የሳይንስ ቤተ ሙከራ ክፍሎች ህይወት ያለውን አገልግሎት እንዲሠጡ የሚደግፋ የአኒሜሽን ቡድኖች ከክልል ትም/ቢሮ እስከ ትም/ቤት ድረስ እንዲቋቋሙና ተገቢውን ድጋፍ እንዲሰጡ ማድረግ
- የትም/መጽሐፍት እና መሣሪያዎች አያያዝና አጠቃቀምን መከታተል
- በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጀውን የትም/ካላንደርን ለተጠቃሚ ትም/ተቋማት ማሠራጨትና በዚሁ መሠረት ትም/ቤቶች እየሠሩ መሆኑን መከታታል
- የትም/ይዘቶች በካላንደሩ መሠረት መጠናቀቅ መቻላቸውን መከታታል፤መጠናቀቅ የማይችሉ ከሆነ ተከታትሎ ተግባራዊ እንዲሆኑ ማድረግ
- ትም/ቤቶች በየክፍል ደረጃው ለየትም/ዓይነቶቹ የተደለደሉ ክፍለ ጊዜያትን/Periods/ በአግባቡ ተክለው መጠቀማቸውን መከታታል
- ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍሎች የሚዘጋጁ ክልል አቀፍ ፈተናዎች በየክፍል ደረጃው የቀረቡ የትም/ይዘቶችን ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ማካተታቸውን መከታተልና ማረጋገጥ
2 የኢኮቴ ዳይሬክቶሬት
በክልሉ የሚገኙ፤ የመጀመሪያ፤ የሁለተኛና የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች፤ ትምህርት በሬዲዮ ማሰራጫ ጣቢያዎች፤ የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች የሚያስፍልጉ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን አሟልቶ በማቅረብን በቅርበት ድጋፍና ክትትል በማድረግ ሁሉም ተማሪዎችና የትምህርት ማህበረሰብ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመማር ማስተማር ስነዘዴ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል ነው፡፡