የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፊ ዋና ዋና ግቦች
- ከዘርፎች ጋር በቅንጅት መስራት
- ት/ቤቶች የሚያገኙትን ገብ በአግባቡ እንድጠቀሙ በመመሪያዎች ላይ ግነዛበ መስጠትና መደገፊ
- ከቢሮ ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ የት/ቤቶች ግነባታን በአግባቡ መደገፍነና የክፊል ተማር ጥምረታዎችን ማስተካከል
- የት/ት ብክነት እነዳይከሰት መመርያዎችንና ድነቦችን ተግባር እንሆኑ መከታተል
- በ ሁሉም ት/ቤቶች የሚገኙ ተማርቸዎች ልዩ ፍላጎት ያላቸዉ ጨምሮ ፆታዊ ልዩነት እንዳይኖር በማድረግ ማስራት
- ለት/ት ጥራት የሚሆኑ ሀብቶችን ከመነግሰተሰት፣መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ከህዘብ የሚሰበሰቡት ለታለመለት ዓላማ ላይ እድዉል መከታተልና መደገፍ
- ጥራት ያለዉ መረጃ በመሰብስብና በመትነትነ ወቅቱን በመጠበቅ ለሚመለከተዉ አካል ማስተላለፍ
- የመ/ርን ጥቅማጥቅም በተቀመጠዉ መመርያ መሰረት ተገባራዊ እድሆን መስራትና መከታተል
- ግዠዎችና ወጭዎች በጥራት በወቅትና በታቀደዉ ልክ እድፈፀም በትኩረት ይሠራል
- ለማህበረሰቡ ጥራት ያለዉ ት/ት ለማድረስ ጠናማ የሆነ ማህበረስብ እነድኖር ኤ.ች.ቨ ኤድስ ለመከላከል ጠንካራ የግንዛበ ሥራ መስራት
- ጥራት ያለዉ ት/ት ለማረጋገጥ በሙያዉ የታመነ ፤በሥነ ምግባር የታነፀ ባለሙያን በግለፀኝነትና በፍታዊነት መቅጠር
- የት/ቤቶች አመራር በብቃታቸዉና በዉጠታቸዉ መሠረት እንድመደቡ በትጋት ይሠራል
1 የሰዉ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የዳይሬክቶሬቱን ሥራ በማቀድ፣ በመምራት፣ በማስተባበር፣ አፈጻጸሙን በመከታተልና በመገምገም ሥራውን ውጤታማ ማድረግ
• የዳይሬክቶሬቱን ተግባራት ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል ይቆጣጠራል፣ የስራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ ክፍተቶችን ይለያል፣ ያበቃል፣
• ከዘርፉ ስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣
• የተቋሙን ሠራተኞች መንግሥት በወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ በምዘናው ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን ያከናውናል፣
• በተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በሰው ሃብት ሥራ አመራርና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት ይከታተላል፣
• በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የዲስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፣
• አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፣
• የዳይሬክቶሬቱን ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ለበላይ አካል ሪፖርት ያቀርባል፣
2 የመምራንና የትም/ት አመራር አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
በመከታተልና በመገምገም ሥራውን ውጤታማ ማድረግ፣
• የዳይሬክቶሬቱን ተግባራት ያቅዳል፣ ያደረጃል፣ ይመራል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል ይቆጣጠራል፣ የስራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ ክፍተቶችን ይለያል፣ ያበቃል፣
• ከዘርፉ ስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣
• በሴክተሩ የሚገኙ ሠራተኞች መንግሥት ባወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ በምዘናው ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን ያካናውናል፣
• በተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በመምህራን፣ በትምህርት አመራርና በሠራተኞችአስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት ይከታተላል፣
• የመምህራን፣ የትምህርት አመራርና ሌሎች ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች በማዘጋጀትና በማሻሻል በሴክተሩ የመምህራንና የትምህርት አመራር ድልድል/ ምደባ፣ ዝውውር የቅሬታ ማስተናገጃ እንዲሁም በሴክተሩ ለሌሎች ሠራተኞች ደግሞ ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የድስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፣
• አዲስ ለሚደለደሉ/ ለሚቀጠሩ ዕጩ መምህራንና የትምህርት አመራር/ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፣
የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት
- የትምህርት ሴክተሩን ፖሊሲንና ስትራቴጂ መነሻ ያረገ የትምህርት ልማት ዕቅድና ሪፖርት ማዘጋጀት
- በበጎ አድራጊዎችና በሕብረተሰቡ ተሳትፎ በተገኘ ገነዘብ የሚገነቡ ግንባታዎች በወቅቱነና በጥራት ተሰርቶ መጠናቀቁን መከታተል ማረጋገጥ
- የበጀት ስረዓትን ማስተዳደር
- በመንግስት በሚመደብ መደበኛና ካፒታል በጀት የሚሰሩ ስራዎች ወይም ተግባራት አፈጻጸምን በማሻሻል የሴክተሩን አቅም ማጎልበት
- ከማሕበረሰብና መንግሰታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ሀብት በማፈላለግ የሴከተሩን አቅም ማጎልበት
- መንግስታዊ ላልሆኑ የበጎ አድራጎት ተቀማት አስፈላጊ ድጋፍ ማድረግ
- በትምህርት ላይ የሚሰሩ የበጎ አድራጎት ተቀማትና ማህበራትን መደገፍና መከታተል
- የትምህርት ሴክተሩን የዕቅድ አፈጻጸም መከታተልና መገምገም
የዘርፈ ብዙ ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት
በክፍሉ የምሰሩ ሥራዎች
- የትምህርት ማህበረሰብናለሎች ዘጎች በኤች.አይ.ቪ/ኤዲስ እና በአባላዘር በሽታ እንዳይያዙና እንዳይጠቁ ማስተማር ወይም ግንዛቤ መፍጠር፡፡
- በሁሉም ትምህርት ቤት የተጠናከረና የተደራጀ የፀረ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ክበባትን ማቋቋምና ተንክረዉ መልዕክት እንድያሰተላልፉ ማድረግ፡፡
- ኮንደም ማሰራጨት ፣ አጠቃቀምና አገልግሎቱን ማስተዋወቅ፡፡
የበሽታዉ መተላለፍያ መንገዶች
- ሊቅ የሆነ የግብረ ሥጋ ግኑኝነት
- ስለታማ ቁሳቁሶችን በጋራ በመጠቀም
- የዉርስ ጋብቻ፣ድርብ ጋብቻ…….ወዘተ
በሽታዉን መከላከያ ዘደዎች
- ሊቅ የሆነ ግብረ ስጋ ግንኙነትን(ዝሙትን) ማስወገድ
- ስለታማ ቁሳቁሶችን በጋራ መጠቀምን ማስወገድ
- 1 ለ1 ጋቢቻን ማጠናከር
- ኮንደምን በአግባቡ መጠቀም
ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን በጋራ እንከላከል!!
የሴቶች ህፃናት ጉዳይ ማካተትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት
በሥራ ሂደቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች
• የሥራዓተ ጾታ ክፍተት መለየት
• የማስፈጸሚያ መመሪያዎችን የአሰራር መኑዋሎችን ማዘጋጀት/መከለስ/
• ስልጠናዎችን ማዘጋጀትና መስጠት
• በፈጻሚ አካላት መካከል ቅንጅት መፍጠር
• ረቅቂ ዕቅዶችን ከሥርዓተ-ጾታ አንጻር መፈተሸ
• ተሳትፎአቸዉን የሥርአተ ጾታ ኦዲት ማድረግ
• በሥራ ሂደቱ አፈጻጸም ላይ ድጋፋዊ ክትትልና ግምገማ ማድረግ
• በተጠቃሚ ደረጃ በሚመጣዉ ዉጤት ላይ መረጃዎቸወነወ ማዘጋጀትና ማዉጣት
የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
በግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ውስጥ የሚሰሩ ዋና ዋና ስራዎች
- በየወሩ ስራ ማስኬጃ ገንዘብ፡- ደመወዝ እንዲሁም ካፒታል፣ ወሩ በገባ በ10ኛው ቀን ከፋይናንስ ቢሮ ጠይቆ ማምጣት፤
- ልዩ ልዩ መደበኛ በጀት፣ ካፒታል፣ ዩኒሴፍ፣ ዋን ዋሽ፣ ጂኲፕ እና ሌሎች እንዲህ አይነት ክፍያዎች መመሪያውና ደንቡ በሚፈቅደው መሰረት መክፈል፤
- ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ተቀናሽ ግብርና እንደዚሁም ልዩ ልዩ የአደራ ገንዘብ በመሰብሰብ ወሩ በገባ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው በማስተላለፍ ማስረጃ መውሰድ፤
- ወሩ በገባ በ25ኛው ቀን ለሰራተኞች የሚከፈል ፔይሮል በማዘጋጀት ባንክ በመላክ ከ26ኛው ቀን ጀምሮ አፈጻጸሙን መከታተል፤
- በየወሩ ተሰብሳቢ ሂሳብ በጊዜ መወርዱን መከታተል፤
- የበጀት ዝውውር ስራ መከታተልና መመዝገብ፤
- በየወሩ የሂሳብ ስራዎችን በመከታተል ወሩ በገባ እስከ 10ኛው ቀን የባንክን ሂሳብ መከታተል፤
- በየእለቱ የሂሳብ ምዝገባ በአይቤከስ ሶፍትዌር በመመዝገብ ከቀኑ 10፡30 እስከ 11፡30 ባለው ጊዜ ውስጥ በማስተካከል የማጣራት ስራ መስራት፤
- የዜሮ ሚዛን ሪፖርት ወሩ በገባ በ10ኛው ቀን ለክልሉ ፋይናንስ ቢሮ መላክ፤
- በየወሩ ለኦዲት ስራ መረጃ በማዘጋጀት ሂሳቡ እንዲጣራ በማድረግ ስህተት ቢገኝ አፋጣኝ ማስተካከያ ማድረግ፤
- ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በጀቱን በአግባቡ መክፈልና ስሌቱን ማውረድ፤
- አመታዊ እቅድ በማሰባሰብ የግዢ እቅድ ማዘጋጀትና ከሐምሌ 1-30 ባለው ጊዜ ውስጥ ለግዢ ኤጀንሲ መላክ፤
- የግዢ ፍላጎት መሰረት በማድረግ እስፔስፊኬሽን ማዘጋጀት፤
- የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀትና ጨረታውን በአግባቡ ማጠናቀቅ፤
- የቢሮን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ጥራት ያለው እቃ ገዝቶ ማቅረብ፤
- የዋጋ ጥናት መረጃ ለሚፈልግ ማቅረብ፤
- ለተቋሙ ንብረት መለያ ቁጥር መስጠት፤
- እቃዎችን በመልካቸው ለመለየት ስርአት ባለውና በጥሩ ሁኔታ መዝግቦ መከታተል፤
- በሶስተኛው መጨረሻ አመት የንብረት ቆጠራ ማድረግ፤
- የሚጠገኑና የሚወገዱ እቃዎችን በመለየት በመመሪያው መሰረት ማንሳት፤
- ወደ ሳጥን የሚገባና የሚወጣ ሂሳብ በመከታተል መዝገቡን በመልኩና በጀቱን በርእሱ ለይቶ መመዝገብ፤
- በየእለቱ ሳጥኑን ማስቆጠርና አስፈላጊ ሰነዶችን በደንብ መያዝ፤
- የበጀት አመቱን የሂሳብ ሰነድ በወርና በበጀት ምንጭ ግዢና በሌላ በሌላ የክፍያ ሰነድ ለይቶ በሞዴል 42 መዝግቦ መስጠት ወይም መውሰድ፤
- የግዢ አጠቃላይ ውል ማዘጋጀት፣ ማጽደቅና መረጃ መተንተን፤
- የግዢ መረጃ በመልክ መልኩ በመለየት መመዝገብ፣ የግምገማ ውጤት በቦርድ ላይ መለጠፍና ለህዝቡ ይፋ ማድረግ፤
- ጨረታ የሚከፈትበትን ስነ-ስርአት፣ ንብረት መቁጠርና የተበላሸውን ለይቶ የማስወገድ ስራ የስነ-ስርአት ክፍልና ከውስጥ ኦዲት ጋር በቅንጅት መስራት፤
- የተቆጠረውን ንብረት መመዝገብ፤
- ለለውጥ የታሰበውንና የቡድን ስራ ባህል ማሳደግ፤
- የፈጻሚዎችን አቅም መገንባት፤
- የልምድ ልውውጥ ማድረግ፤
- ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረግ፤
1 ስታትስቲክስና መልከአ-ምድራዊ ዳታ ስርዓት አስተዳደር ትንተና ስርጭትዳይሬክቶሬት